Tuesday, September 8, 2015

የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ይፋ ማድረጉን አስታወቀ።
ተማሪዎችም ዛሬ ከቀኑ 8 ስአት ጀምሮ የሞባይል ስልካቸውን በመጠቀም በ8181 ላይ RTA ከዚያ ክፍተት በመስጠት የፈተና መለያ ቁጥራቸውን አስገብተው በመላክ  ወጤታቸውን በነጻ ማወቅ ይችላሉ ተብሏል።
እንዲሁም በኢንተርኔት መከታተል የሚችሉ ደግሞ ከአሁኑ ስአት ጀምሮ በኤጀንሲው የድረ ገጽ አድራሻ www.nae.gov.et/ አልያም www.neaea.gov.et/ በመግባት እና የፈተና መለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ማየት ይቻላሉ።
በ2007 ዓ.ም ከ991 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና የተቀመጡ ሲሆን፥ 669 ሺህ 732 ተማሪዎች 2 ነጥብና ከዚያ በላይ ውጤት ማምጣታቸውን ኤጀንሲው አስታውቋል።
ከእነዚህ መካከልም 14 ሺህ የሚሆኑት 4 ነጥብ አስመዝግበዋል።
- See more at: http://www.fanabc.com/index.php/news/item/10182-%E1%8B%A810%E1%8A%9B-%E1%8A%AD%E1%8D%8D%E1%88%8D-%E1%89%A5%E1%88%84%E1%88%AB%E1%8B%8A-%E1%8D%88%E1%89%B0%E1%8A%93-%E1%8B%8D%E1%8C%A4%E1%89%B5-%E1%8B%AD%E1%8D%8B-%E1%88%86%E1%8A%90.html#sthash.AdJvYFSE.dpuf

No comments:

Post a Comment