ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2008 ዓ.ም የመሰናዶ ትምህርት የመግቢያ ነጥብ ይፋ ማድረጉን አስታውቋል።
በዚህም ለመደበኛ እና የማታ ተማሪዎች ለወንዶች 2 ነጥብ 71 እና በላይ ለሴቶች 2 ነጥብ 43 እና ከዚያ በላይ ሆኗል።
የታደጊ ክልሎችና የአርብቶ አደር አካባቢ ተማሪዎች ለወንዶች 2 ነጥብ 43 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 2 ነጥብና 14 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ለአይነስውራንና መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ለወንዶች 2 ነጥብ 14 እና ከዚያ በላይ ለሴቶች 2 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ሆኗል።
የግል ተፈታኞች ደግሞ ለወንዶች 3 ነጥብ 29 እና ከዚያ በላይ ሲሆን ለሴቶች 3 ነጥብ እና ከዚያ በላይ መሆኑን ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ገልጿል።
No comments:
Post a Comment